ማሻ፤ የካቲት 17/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን ለማዘጋጀት መመረጧን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ።
ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኅን መግለጫ ሰጥቷል።
የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር በአህጉሪቱ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትን የማስተባበር፣ አቅም የመገንባትና እርስ በርስ በማቀናጀት የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚሰራ ነው።
ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ መግለጫውን በሰጡትበት ወቅት እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር በ2019 ዓ.ም የሚካሄደው 16ኛውን ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ውሳኔ ያስተላለፈው በካሜሩን ያውንዴ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን ለማዘጋጀት መመረጧ በሀገሪቷ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ለተከናወኑ ተግባራት እውቅና የሰጠ ነው ብለዋል።
ጉባዔውም ኮሚሽኑ ቀጣይ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ከአቻ ተቋማት ጋር ልምድና ተሞክሮ የሚጋራበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ጉባዔውን ለማስተናገድ የሚያስችል እቅድ አውጥቶ ወደስራ መግባቱን የገለፁት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ለጉባዔው መሳካት የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በታራሚዎች አያያዝ፣ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ የአካል ጉዳተኞች የተጠቃለለ ሕግ ማውጣት የሚያስችል ፖሊሲ ዝግጅትና በማህበረሰብ ድርጅቶች ምኅዳር ላይ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች አያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መሻሻል እንደሚታይባቸውም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የማሻሻያ ሥራዎች ማከናወኑንም አስረድተዋል።
More Stories
የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
በክልሉ የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነት እንዲጠናከር በማድረግ የብሔረሰቦች ፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ፦ አቶ ጌታቸው ኬኒ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ብሔራዊ መግባባትን መገንባት የሚያስችል ወሳኝ አጀንዳ ነው – አምባሳደር ሶፊ ፍሮም- ኤመስበርገር