ማሻ፤ የካቲት 13/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ700 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን በማስተናገድ 2.6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቷን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቱሪዝም ዘርፉ አዳዲስ መዳረሻዎችን በመገንባትና ነባሮችን በማደስ ባሳየው ከፍተኛ መነቃቃት፣ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ ከ700 ሺህ በላይ ጎብኚዎችን መሳብ ችሏል።
ይህ አፈጻጸም ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ግኝት አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ ለውጤቱ መገኘት ታላላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች በአዲስ አበባ መካሄዳቸው ትልቅ ድርሻ ነበረው።
የቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባትና የቱሪስት ፍሰቱን ለማሳደግ ዘመናዊ የዲጂታል የማስተዋወቂያ ስልቶችን በስፋት እየተጠቀመ ይገኛል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)፤ “ቪዚት ኢትዮጵያ” (Visit Ethiopia) የተሰኘው ድረ-ገጽ ቱሪስቶች ወደ ሀገር ከመምጣታቸው በፊት መዳረሻዎችን በቀላሉ እንዲመርጡ እያገዘ መሆኑን ለኢቲቪ ገልፀዋል።
ድረ-ገጹ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ በመሆኑ፣ ጎብኚዎች የሆቴልና የጉዞ መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አንስተዋል።
በተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ባሮሜትር መለኪያ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም እ.አ.አ በ2025 የ15 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፍ የቻለ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ በዘርፉ የጀመረችው የሪፎርም ሥራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ማሳያ ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል
More Stories
ዋሽግተን-ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕን የቀረጥ ጭማሪ ደንብ ዉድቅ አደረገ
የገቢ አቅማችንን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም የአመራሩንና የፈፃሚውን የሥነ-ምግባር ክፍተት መቅረፍ ይገባል፦ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር የተጀማመሩ የልማት እንቅስቃሴዎች ህዝቡንና መንግስትን የሚያስተሳስሩ በመሆናቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል