ማሻ፤ የካቲት 13/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የቴፒ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጥላሁን ዳቃ በጉባኤዉ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት
የምክር ቤቶችን አሰራርን ተከትሎ ጉባኤዎችን በተቀመጠዉ የጊዜ ሰለዳ ማካሄድ እና የህዝብ መድረኮችን በመፍጠር እና ሴክተር መስሪያ ቤቶችን በመደገፍ በመከታተልና በመቆጣጠር በትኩረት እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል ።
በ2018 በከተማዉ የተጀመረዉ የልማት እንቅስቃሴ የህዝብና የመንግስት ግንኙነትን የሚያጠናክር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባዉም አዉስተዋል።
የአሁኑን ጉባኤ ለየት የሚያደርገዉ በህዝብ ተሳትፎ በቴፒ ከተማ የዉስጥ ለዉስጥ አስፖልት ለመገንባት ገቢ የማሰባሰብና መሰል ተግባራት ዙሪያ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ማግስት እና ለ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት እየተደረገበት ባለ ወቅት መሆኑን ዋና አፈ ጉባኤዉ ጠቁመዋል።
በጉባኤዉ የምክር ቤቱ የባለፈዉ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በምክር ቤቱ አባላት ሙሉ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን የምክርቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የባለፈዉ 6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት በምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ በወይዘሮ መሠረት ተስፋዬ ቀርቦ በአባላቱ ምክክር እየተደረገበት ነዉ።
ምክር ቤቱ ዛሬን ጨምሮ በ2 ተከታታይ ቀናት ዉሎ የከተማ አስተዳደሩ፣የቴፒ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የባለፈዉ የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ምክክር የሚደረግ ሲሆን የከተማዉ ማዘጋጃ ቤት ምጣኔ ማሻሻያ ተመን እና የከተማ ቦታ ደረጃ ጥናት ሰነድ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ተገልጿል።
በከተማዉ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች በምክር ቤቱ አባላት ተጉብኝቶ ጉባኤዉ መቋጫዉን እንደሚያገኝም ተመላክቷል
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር የተጀማመሩ የልማት እንቅስቃሴዎች ህዝቡንና መንግስትን የሚያስተሳስሩ በመሆናቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
More Stories
ዋሽግተን-ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕን የቀረጥ ጭማሪ ደንብ ዉድቅ አደረገ
ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፉ 2.6 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘች
የገቢ አቅማችንን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም የአመራሩንና የፈፃሚውን የሥነ-ምግባር ክፍተት መቅረፍ ይገባል፦ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ