ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) አርሶ-አደሮች በፍጹም ጽናት፣ ቅንጅት እና ትብብር አካባቢያቸውን የቀየሩበትን ስራ በመመልከታቸው መደሰታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።
የተመለከቱት የእርሻ ስራ ፤ የአካባቢ መሬትን እና የውኃ ኃብትን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።
ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በቅርብ ያለ ኃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ በማዋል ማኅበረሰቡ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከል መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
በተለይም የመንገድ መሠረተ-ልማት የአርሶ-አደሮችን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ የፈጠረውን እድል መመልከት እጅግ የሚያበረታታ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ይኽ እድገት የልማት ጥረቶች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ፍላጎት እና አቅም ጋር በቅርበት ሲናበቡ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑንም አመላክተዋል።
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ