February 18, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ግልጽ ፣ቀልጣፋና የዘመነ እንዲሆን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ

ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ማዘጋጃ ቤቱ በገቢ አሰባሰብ ፣ በመሬት ዘርፍ ፣በኮንስትራክሽን፣ በካዳስተር እና በሌሎችም ዘርፎች የአገልግሎት ማዘመኛ ዲጂታላይዜሸን ሶፍትዌር ሲስተም ስራዎችን በማስጀመር ለሌሎች ልምድ የማካፈል መረሃ ግብር ተከናውኗል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ  አቶ አክሊሉ ተገኝ እንደገለፁት በማዘጋጃ ቤቶች የዘመነ አገልግሎቶች እንዲሰጥ ለማስቻል ዲጂታላይዜሸን ሶፍትዌር ሲስተምን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል ።

በቴፒ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ የተገልጋዩን እንግልት የሚያስቀር በመሆኑ በሌሎችም አካባቢዎች ላይ የማስፋት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል ።

የከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ለማስቻል ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ደመላሽ ገዳ ናቸው ።

የቴፒ ከተማ ማዘጋጀት ቤት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ይስማው በበኩላቸው አገልግሎት መጀመሩ ጊዜን፣ ገንዘብንና ጉልበትን በመቆጥብ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሶፍትዌር መሆኑን ገልፀዋል ።

በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ የማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጆችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ቴክኖሎጂው በአገልግሎት አሰጣጥ ህደት ውስጥ የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮችን የሚቀርፍ በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ ሲለ መሆናቸው ጠቁመዋል