ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
ስልጠናው የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ከክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ነው፡፡
በስልጠናው የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ሰልጠናውን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ ኡሮ አስጀምረዋል፡፡
የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ፣ የመንግስት አስተዳደር ፖሊሲ የትኩረት መስኮችና የያዛቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የስልጠና ሰነድ እያቀረቡ ነው፡፡
#ቦንጋ ኤፍ ኤም
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ