ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ኢትዮ ቴሌኮም ከአገር ውስጥ ገበያ ባለፈ አገልግሎቶቹን በቀጠናው በማስፋፋት ለአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የማበርከት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (AFC) ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳማይላ ዙባይሩ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም የተቋሙን ራዕይና ፍላጎት ጠቅሰው፥ ይህን ዕውን ለማድረግ ጠንካራና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተቋሙ ከዚህ ቀደም የተገበራቸው ስትራቴጂዎች የተቋሙን ጠንካራ የመፈጸም አቅም በተግባር ያረጋገጡ መሆኑን አስረድተዋል
#አራዳ ኤፍ ኤም
More Stories
ሶማሊያ በአሜሪካ ድጋፍ በአል-ሸባብ ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ ማጠናከሯ ተገለጸ።
ዝነኛው ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሞያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ተሸለሙ።
ሦስት አዳዲስ የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማሪፊያዎች በቅርቡ አገልግሎት ይጀምራሉ