February 18, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ(ፕላስቲክ) አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ዙሪያ በቴፒ ከተማ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።

ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የቴፒ ከተማ  ግብርና  አካባቢ  ጥበቃ ህብረት  ሥራ ልማት ጽ/ቤት  በደረቅ ቆሻሻ  አያያዝና  አወጋገድ  (ፕላስቲክ ) አዋጅ ዙሪያ  ለባለድረሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ  ሥልጠና ተሰጥቷል ።

‎ የሸካ ግብርና አካባቢ  ጥበቃ ህብረት  ሥራ ልማት  መምሪያ  የአካባቢ  ጥበቃ አየር  ንብረት  ለውጥ  ቡደን መሪ አቶ አጥናፉ   ደግፌ የፕላስቲክ ማምረትና መጠቀምን ለመከላከል በወጣው በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ዙሪያ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች በህብረተሰቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች እንዲሁም በአፈር ለምነት፣ በውሃ እና አየር ንብረትን በመበከል ጉዳት የሚያደርሱ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎ እነዚህ የፕላስቲክ ምርቶች የሚያደርሱትን አደጋ ህብረተሰቡ ከግምት ውስጥ በማስገባት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ የወጣውን አዋጅ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አስገንዝበው ፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚያመርቱ አምራቾች አካባቢን የማይበክሉና ተተኪ ምርቶችን በማምረት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።


‎የቴፒ ከተማ  ግብርና  አካባቢ  ጥበቃ ህብረት  ስራ ልማት ጽ/ቤት  ኃላፊ አቶ አየለ አለማየሁ እንደገለፁት የፕላስቲክ አጠቃቀምን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የወጣውን አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡም ፕላስቲክን ከመጠቀም በመቆጠብ አካባቢውን ከብክለት መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

‎በውይይቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ት ፕላስቲክ(ፌስታል) ለመሬትና ለሰው ልጅም አደጋ መሆኑን ተናግረው የወጣውን አዋጅ  የማስገንዘቡና አዋጁን ተግባራዊ  የማድረጉ ሥራ  ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል ።

‎በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 መሰረት የፕላስቲክ ከረጢቶችን የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘና  የሚሸጥና የሚለውጥ ማንኛውም ግለሰብ  በህግ የሚያስጠይቅ ጠቁመዋል