የካቲት 9/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የትግራይ ለውጥ ፈላጊዎች ንቅናቄ “ሰላም ለህዝባችን፣ ለውጥ ለወደፊት ተስፋችን” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከክልሉ ተወላጆች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
በምክክሩ ላይ የተሳተፉ የንቅናቄው አመራሮችና የክልሉ ተወላጆች ከሻዕቢያ መንግሥት ጋር በማበር የሚመለስ የሰላምም ሆነ የልማት ጥያቄ አለመኖሩን በአጽንኦት ገልጸዋል።
የንቅናቄው አባልና የሰላም ስምምነቱ ተደራዳሪ አቶ አሰፋ አብርሃ፤ ጥቂት የቀድሞ ሕወሓት አንጃዎች ከሻዕቢያ ጋር በመሰለፍ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥትን እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት እየጣሱ መሆኑን ገልጸዋል። ድርጊቱንም “ባንዳነት” ሲሉ ፈርጅውታል።
ሌተናል ጀኔራል ጻድቃን ወልደትንሣኤ በበኩላቸው፤ የፌዴራል መንግሥት ተፈናቃዮችን ለመመለስ እንቅፋት ሆኖ እንደማያውቅ ጠቅሰው፣ የቀድሞው ሕወሓት አንጃ ግን ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት በማዋል ለስምምነቱ መስተጓጎል ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።
የትግራይ ሕዝብ ከጥፋት ቀጣና ለመውጣት ጦርነትን ሊቃወም እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በክልሉ አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ሕጋዊ መንግሥት እንዲመሰረት መሥራት የንቅናቄው ዋነኛ ዓላማ መሆኑ ተገልጿል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የትግራይ ሕዝብ ዋነኛ ጥያቄ ሰላም እና ልማት መሆኑን በመጥቀስ፤ ችግሮች የሚፈቱት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በሰላማዊ መንገድ በመተባበር እንጂ ከውጭ ኃይሎች ጋር በመወገን እንዳልሆነ አፅንዖት መስጠታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ