ማሻ፤ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የአህጉሪቱን የፋይናንስ መዋቅር ማጠናከርን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት በአዲስ መልክ ለማደስ እንደሚሰሩ አስታወቁ።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ባንኩ ለአፍሪካ ቁልፍ የትኩረት መስኮች እያደረገ ያለውን ጠንካራ ድጋፍ ያደነቁ ሲሆን ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 11 ቢሊን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን መልካም የሚባል እርምጃ መሆኑን አመልክተዋል።
ሊቀመንበሩ እና የባንኩ ፕሬዝዳንት ከእዳ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የደህንነት ፈተናዎች ባለፈ የፋይናንስ አቅርቦት የአፍሪካ አበይት ፈተና መሆኑን በምክክራቸው ወቅት ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች የፕሮጀክት ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር፣ የአንድ ትሪሊን የአሜሪካን ዶላር የአፍሪካ ካፒታል ማሰባሰብ፣ የአፍሪካ የብድር ምዘና ኤጀንሲን ማጎልበትና ጠንካራ የአፍሪካ የፋይናንስ ስርዓት መገንባት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ ተሠማመተዋለ።
በዓመት ሁለት ጊዜ ለመወያያት እና በአፍሪካ ፋይናንስ ላይ የከፍተኛ ደረጃ ምክክር ለማካሄድ እቅድ መያዛቸውንም ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር የጀመረው የሰንበት ገቢያ በበዓል ወቅት ከሚፈጠረው የዋጋ ንረት ታድጎናል ሲሉ የሸካ ዞን ማሻ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።