ማሻ፤ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) መንግስት የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት አዳዲስ መመሪያ በማዘጋጀትና የተለያዩ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።
በዚህም የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት የማሕበረሰቡን ኑሮ ጫና ማቃለል እንዲያስችል የሰንበት ገበያዎች ተቋቁመው ማሕበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው።
ሰንበት ገበያው የተለያዩ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን ከአምራቾች ወደ ሸማቹ ቀጥታ በማድረስ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር ያግዛል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት የሰንበት ገበያ ማጠናከር ይረዳ ዘንድ 3 ሚሊዮን 845 ሺህ ብር ተመድበው ሥራዎች ሲሰሩ መቆየቱን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታውቀዋል
#ሪፖርታዥ
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ