ማሻ፤ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ኪንግደም መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱንም ገልጸዋል።
በቅርቡ የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ የልማት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር የመጀመሪያውን የአፍሪካ ጉብኝት በኢትዮጵያ መጀመራቸውን አስታውሰዋል።
ይህም የሀገራቱ ወቅታዊ ግንኙነት እያደገ ለመምጣቱ ታላቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚሁ ወቅትም የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስምምነቶች መፈረማቸውን አብራርተዋል።
ለዩናይትድ ኪንግደም በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም መኖሩን ጠቁመው፣ ይህንን ዕድል ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ ለጎረቤቷ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እየከፈለችው ለሚገኘው መስዋዕትነት ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሶማሊያ እያከናወነችው ያለው ተግባር የሀገሪቱን ታላቅነት እና ለጎረቤቶቿ የምትሰጠውን ታላቅ ስፍራ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሰፊ የልማት አቅም ያለው የአፍሪካ ቀንድ ወደ ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና እንዳላትም ጠቅሰዋል።
ቀጣናው ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና ፀጥታ ወሳኝ ሚና እንደምትጫወት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰፊ የሕዝብ ቁጥር ያላት፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያስመዘገበች ያለች እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት በጎ አስተዋጽኦ የምታበረክት ሀገር ናት ብለዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደረገውን ጥረት እንደሚረዱ ገልጸው፣ የባህር በር ለማገኘት የያዘችውን ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠቁመዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ኢንቨትመንት እና ንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እየሠራች ስለመሆኑም ማብራራታቸውን ፒኦኤ ዘግቧል።
More Stories
የናይጀሪያ ጥቃት
ኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፉን የምትገነባ እና የምትመራ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
በአፍሪካ የሥራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የፓን አፍሪካ የኢኖቬሽን ኮሪደር መፍጠር ይገባል፡- ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ