የካቲት 9/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በስኮትላንድ የግላስጎው የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው የ22 ዓመቷ ኤሚሊያ ኢቫንስ-ሙንተን፣ የዓለማችን ግዙፉን የጦጣ ቅርጽ ያለው (Sock Monkey) የአሻንጉሊት ቅርፅ በመሥራት ጊነስ ዓለም አቀፍ ክብረ ወሰን ላይ ተመዘገበች።
ይህ ግዙፍ አሻንጉሊት 15 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ ለሥራውም 60 ሜትር ገደማ የሚረዝም ጨርቅ እና የተለያዩ ግብዓቶች ጥቅም ላይ ውለዋል።
ወጣቷ አርቲስት ሥራውን የሠራችው ትልልቅ ሰዎች ከግዙፉ አሻንጉሊት አንጻር ሲታዩ ራሳቸውን እንደ ሕፃን እንዲቆጥሩና የልጅነት ስሜታቸው እንዲቀሰቀስ ለማድረግ እንደሆነ ገልጻለች።
ይህ ግዙፍ አሻንጉሊትበእንግሊዝ ኖርፎልክ በተካሄደ የጥበብ ፌስቲቫል ላይ ለሕዝብ የቀረበ ሲሆን፣ ጎብኚዎች አሻንጉሊቱን በመንካት እየተጫወቱ እንዲዝናኑ ተደርጓል ሲል የዘገበው ዩፒአይ ነው።
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ