ማሻ፤ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በምርጫ ወቅት ለሚነሱ ቅሬታዎች በሕግ ላይ የተመሠረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ገለፁ።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር፣ በምርጫ ጉዳዮች ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
በምርጫ ሂደት ለሚነሱ ቅሬታዎች አፋጣኝ የፍትሕ ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓትን በመፍጠር በኩልም ዳኞች ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል።
ምርጫ ዜጎች የሚመራቸውን አካል የሚመርጡበት ታላቅ ሀገራዊ ሂደት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ሂደቱ ፍትሃዊ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል ።
በቀጣይ በምርጫ ሂደት የሚነሱ ቅሬታዎችን በሕግ ላይ የተመሰረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ነው ፕሬዚዳንቱ ያረጋገጡት።
ለዚህም ዳኞች ለምርጫው ስኬታማነት የሚኖራቸውን ድርሻ ለማላቅ ሂደቱን ማስገንዘብ የሚያስችል ስልጠና መስጠት እንዳስፈለገ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወረቅ ሃይሉ ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ምርጫው ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተቀመጡ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ በቂ ግንዛቤ መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተለይም በቅሬታ አቅራቢና በቅሬታ ፈቺ አካላት መካከል ወጥ የሆነ መረዳት ለመፍጠር ስልጠናው ጉለህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ስልጠና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን፣ በምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች እና በሰበር ሰሚ ዳኞች የሚሰጥ ሲሆን በሶስት ዙር 150 ዳኞች እደሚሳተፉ በመድረኩ ተገልጿል ሲል የዘገበው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው
More Stories
የናይጀሪያ ጥቃት
ኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፉን የምትገነባ እና የምትመራ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ያላሰለሰ ጥረት እና የምትከፍለውን መሥዋዕትነትም አድንቀዋል።