ማሻ፤ የካቲት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በደቡብ ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ሠላም በር ቀበሌ ከሠላም በርመንደራሻዲካይ ያለው 3 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ በህብረተሰብ ተሳትፎ በ2 ሚሊዮን 58 ሺህ ብር EATL በተሰኘ ተቋራጭ ተገንብቶ በዛሬው ዕለት ለምረቃ በቅቷል።
የክልሉ ከተማጨልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ፣የሸካ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መመምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀራ እና የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ተሰማ በጋራ ሪቫን በመቁረጥ መንገዱን አስመርቀዋል።
የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ተሰማ በመንገድ ምረቃው ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በ2017 ዓ.ም ሰፊ ንቅናቄ በማድረግ ከህብረተሰቡ ተሳትፎ በተሰበሰበ 2 ሚሊዮን 58 ሺህ ብር 3 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ ዛሬ ለምረቃ መብቃቱ የአካባቢውን ህብረተሰብ የመንገድ ችግር ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
የሸካ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መመምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታም ሀራ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ላይ ለምረቃ የበቃው ከሠላም በርመንደራሻ ዲካይ ያለው 3 ኪሎ ሜትር መንገድ ለአካባቢው ህብረተሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ በፍጥነት መኪኖች እንዲመደቡ ይደረጋል ብለዋል።
በመንገድ ምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የመንገድ ስራው ለምረቃ እስኪበቃ ድረስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ሽልማትና ምስጋና ተችሯቸዋል።
አንዳንድ የአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት የምናመርተውን ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬ፣ ቅመማ ቅመም እና አትክልት ወደ ገበያ ለማውጣት መንገዱ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
በመንገድ ምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ክልል፣ የሸካ ዞን፣ የየኪ ወረዳ የስራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል ሲል የዘገበው የኪ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ