ማሻ፤ የካቲት 04/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የብልጽግና ፓርቲ አዲስ የምርጫ ምልክቱን ይፋ አደረገ።
ብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክት ዛሬ ባካሄደው የፓርቲው ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ይፋ አድርጓል።
ፓርቲው ግንቦት24/2018ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ፥ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጾ፥ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት የ ”ስንዴ ነዶ” ብልጽግና ፓርቲ የሚወዳደርበት ምልክት መሆኑን አስታውቋል።
ስንዴ የምርታማነት መገለጫ በመሆኑ፥ ፓርቲው በሁለንተናዊ መንገድ የምርታማነት ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንደሚሰራ አስታውቋል።
ስንዴ የመደመርና የመሰናሰል ውጤት በመሆኑ የስንዴ ነዶን የምርጫ ምልክት ማድረጉን የጠቀሰው ፓርቲው ፥ኢትዮጵያን በብልጽግና ጉዞ ከፍ ለማድረግና ለማሰናሰል እንደሚሰራ ገልጿል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያን ከተረጂነት ቀንበር ለማላቀቅ እንደምልክት ተወስዶ በርካታ ስራዎች የሚከወኑበት ነውም ተብሏል።
ፓርቲው ”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” የሚል መሪ ቃልን ያነገበ ባለ 169 ገጽ ማንፌስቶ ይፋ ያደረገም ሲሆን፥ የፓርቲውን የትላንት ስኬቶይ የነገዋን ኢትዮጵያ በብልጽግና ጎዳና ለማራመድ የተያዙ ውጥኖች በዝርዝር ያካተትኩበት ነው ብሏል ።
ትላንትን ማከም፤ ነገን መተለም፣ ፍትሀዊት ኢትዮጵያ ፣ ባለ ሚዛን ኢትዮጵያውያዊነት፣ ከእዳ ወደ ምንዳ የተሻገረ ኢኮኖሚ፣ከውሃ እስከ ውሃ ፣ የጸና ሰላም፣ የቀና ስርዓት 15 ምዕራፎችን በያዘው የፓርቲው ማንፌስቶ ከተካተቱ ምዕራፎች መካከል ናቸው።
More Stories
መንግሥት የብሔረሰቦች ባህል፣ ቋንቋና መልካም ዕሴቶች እንዲታወቁና እንዲጎለብቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን የከጪ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቋል
በሀገር እድገት ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ማጉላት ይገባል ተባለ