ማሻ፤ የካቲት 04/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ክልሉ ከተቋቋመ ወዲህ መሠረታዊ የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገለግሎት መብቃታቸውን ርዕስ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለፁ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን የከጪ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከተቋቋመ ወዲህ መሠረታዊ የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገለግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል።
በተለይ በከጪ አከባቢ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተከናወኑ ተግባራት የኔትወርክ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር መፈታታቸውን ያስረዱት ርዕሰ መስተዳድሩ የባንክና የመንገድ መሠረት ልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አከባቢው ለሁሉም የግብርና ምርቶች ተስማሚ ስለሆነ በአከባቢው ያለውን የመልማት አቅሞችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
አርሶ አደሮች ዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲሁም በህብረት በመደራጀትና የባንክ ብድር በመውሰድ የተሻለ ምርት ለማግኘት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
በአከባቢው ያሉ ወጣቶች በተለያዩ መንገዶች ወደ ስራ ተሰማርተው ሀብት እንዲያፈሩ የክልሉ መንግስት ከዞንና ከወረዳ የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።
የክልሉን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሽፋን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው ናቸው።
ፕሮጀክቱ በክልሉ መንግስት ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት እንደበቃም ተናግረዋል።
የከጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አስተማማኝና ዘላቂ መሆኑን የገለፁ ኢንጂነር በየነ ፕሮጀክቱ የትምህርትና ውሃ ተቋማትን ጨምሮ ከ11 ሺ በላይ የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ከ11 ሺ በላይ የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ዳዊት የአከባቢው ህብረተሰብ የውሃ ፕሮጀክቱን ጠብቀው በተገቢው እንዲጠቀሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለውሃ ፕሮጀክቱ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
More Stories
መንግሥት የብሔረሰቦች ባህል፣ ቋንቋና መልካም ዕሴቶች እንዲታወቁና እንዲጎለብቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት- ”የስንዴ ነዶ”
በሀገር እድገት ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ማጉላት ይገባል ተባለ