ማሻ፤ የካቲት 04/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ”በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች አባላት የውይይት መድረክ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማሻ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ እንዳሻው
የብልፅግና ፓርቲ መንግስት ሆኖ ሀገርን መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንደ ሀገርም ሆነ እንደክልል ብሎም በዞንና በከተሞች ሰፊ የሆነ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ መመዝገቡን ተናግረዋል።
በ2018 ዓ.ም 7ተኛ ዙር ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ፣ነፃ፣ገለልተኛና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሴቶች በነቃ ተሳትፎ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለፀጋ አየለ እንደገለፁት ሴቶች ዘላቂ ሰላምን በማምጣት፣ በሀገረመንግስት ግንባታ ጉዞ፣ሀገራዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ፣ አምራችነትን ከማስፋት አንፃር በግብርና ልማት፣በአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ዓይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት ላይ፣ በቱሪዝም ዘርፍ፣የዲጅታል ኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ላይ፣በከተማ ልማት ስራዎች፣ የሴቶች የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት ላይ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የሴቶችን ሁለንተናዊ ደህንነታቸው ተጠቃሚነት ላይ መብታቸውን ማስከበር፣ ሴቶች በአመራነተና በውሳኔ ሰጭነት ላይ ተሳትፏቸው እንዲጎለብት በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይና ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፋበት መሆኑንም ገልፀዋል።
ሁሉም ዜጋ የዜግነት ግደታውን ለመወጣት ሴቶች በ2018 ዓ.ም በሚደረገው የሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ላይ የሴቶች ሚና ጎልቶ እንዲታይ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት ለሴቶች ባመቻቸው እድል በሌማት ትሩፋትና በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ባሉት ተግባራት ላይ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ማጠቃለያ ያደረጉት የሸካ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አካልነሽ አየነውና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለፀጋ አየለ
የሴቶችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ ያለ በመሆኑ በክልሉ የትምህርት ተጠቃምነትን በሚመለከት በትምህርት ሚንስቴር በኩል ለመቶ ሴቶች የተሰጠ መሆኑን ተናግረው ዘመኑ ድጂታል እየሆነ በመምጣቱ ሴቶችም የዚህ እድል ተጠቃሚ እይዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሴቶች መብቶቻቸውን ለማስከበር ይሆነኛል ይበጀኛል ያሉትን የምርጫ ካርድ በመውሰድ መምረጥና ቀስቅሶ ማስመረጥ እንደሚገባም አስገንዝበዋል
More Stories
መንግሥት የብሔረሰቦች ባህል፣ ቋንቋና መልካም ዕሴቶች እንዲታወቁና እንዲጎለብቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት- ”የስንዴ ነዶ”
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን የከጪ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቋል