ማሻ፤ የካቲት 4/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የማጃንግ ብሔረሰብ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ፓናል ውይይት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሲምፖዚየሙ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለፁት በፌደራሊዝም ሥርዓት ውስጥ ህብረብሔራዊ አንድነት እንዲጠናከርና የብሔረሰቦች እኩልነት እንዲረጋገጥ መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።
በዚህም የብሔረሰቦች ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ እንዲታወቅና እንዲለማ እየተሰራ ያለው ስራ ማሳያ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የማዣንግ ብሄረሰብ ባህል ፣ቋንቋ እና ታሪክ እንዲጎለብት የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
የማጃንግ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮናስ አበበ በበኩላቸው የማጃንግ ብሄረሰብ የራሱ የሆነ ባህል ፣ታሪክ ፣ቋንቋ እና መልካም ዕሴቶች ያሉት ብሄረሰብ መሆኑን ገልፀዋል ።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ገላትያ ሻሜ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክት በማስተላለፍ የማጃንግ ብሄረሰብ ባህል ፣ቋንቋ እና መልካም ዕሴቶች እንዲለሙና እንዲጎለብት በትኩረት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል ።
በሲምፖዚየሙ ላይ በብሔረሰቡ ቋንቋና ባህል ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ፅሁፎች በክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው እየቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ መነሻ ውይይቶች ይደረጋሉ ።
በሲምፖዚየሙ ላይ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መሠረት ማቴዎስ ፣ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ ከጋምቤላ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቡ ተወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች ፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የሌሎችም ብሔረሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው
More Stories
ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ትርጉም አልባ ያደርገዋል አለች
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ