February 9, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በ68 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባዉን የባቹማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ  ተመረቀ

ማሻ፤ የካቲት 2/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ መንግስት በጀት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን የባቹማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።

የኮሌጁ ግንባታ በ2011 ዓ/ም በቀድሞው የደቡብ ክልል ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የተቋረጠ ሲሆን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት በ2017 ዓ/ም ውሉን እንደገና በማሳደስ ግንባታውን በድጋሚ በማስጀመር ቅርብ ድጋፍና ክትትል በማጠናከር በአንድ ዓመት ውስጥ ግንባታውን አጠናቅቆ ለምረቃ አብቅቷል።

በመርሐግብሩ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ፣ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የክልሉ መ/ኮ ነው