ማሻ፤ የካቲት 2/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ (ዶ/ር) በካፋ ዞን የቢጣ ዳካ መንገድ፣ የሜኒ ወንዝ ድልድይ እንዲሁም የቢጣ ገነት ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል።
የቢጣ ዳካ መንገድና የሜኒ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት 94 ሚሊዮን ብር በክልሉ መንግስት እና 4 ሚሊዮን ብር በህብረሰተብ ተሳትፎ በአጠቃላይ በ98 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን መንገዱ 51 ኪሎሜትር ሲሆን ድልድዩ 22 ርዝሜት አለው።
የመንገዱ ግንባታ የአካባቢውን ህብረተሰብ የትራንስፖርት ችግር የሚቀነስ ፣ ገበሬዎች ምርትን ወደ ገበያ በቀላሉ እንዲያደርሱ እና ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ያለውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ጉልህ ሚና ይጫወታል።
በተመሳሳይም ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የቢጣ ገነት ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በ14.4 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ከ19 ሺህ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ጨምሮ የክልልና የካፋ ዞን አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ዘገባው የክልሉ መ/ኮ ነው
More Stories
ውስጣዊ ሰላምን ማፅናት፦ ወቅቱ የሚጠይቀው አርበኝነት
ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በ68 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባዉን የባቹማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ተመረቀ
የዲዚ ብሔረሰብ ማህበራዊ ድልብ ሀብቶችን ለክልላዊ አንድነትና ልማት ማዋል ይገባል፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)