ማሻ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የኤርትራ መንግሥት በቀይ ባሕር አፋር ሕዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት እና የመብት ጥሰት እየፈፀመ ነው አሉ የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን።
ሊቀመንበሩ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷የኤርትራ መንግሥት በአፋር ሕዝቦች ላይ ከሕግ ፍርድ ውጭ ግድያ፣ የዘር ማጥፋት፣ ማሰርና ማሰቃየት፣ በግዳጅ ወታደራዊ ምልመላና በግዳጅ ማፈናቀል ፈጽሟል።
በቀይ ባሕር የአፋር ሕዝቦች የኃይማኖት ነፃነት እንዳይኖራቸው እና በቋንቋቸው እንዳይማሩ ተከልክለው ጫና እየተደረገባቸው እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም በቀይ ባሕር ላይ ዓሣ እንዳያጠምዱ መደረግን ጨምሮ ከምንም አይነት እንቅስቃሴ መታገዳቸውን ነው ያስረዱት፡፡
የአፋር ተወላጆችን በአሰብ ከተማና ሌሎች አከባቢ የማፈናቀል፣ ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የማግለል፣ ወጣቶችን የማሰቃየት፣ የማፈንና ለረጅም ዓመታት በድብቅ ቦታዎች በእስራት የማሰቃየት ድርጊት መፈጸሙንም ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም የኤርትራ መንግሥት የሐይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችን በመግደል ሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸም ላይ ይገኛል ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፡፡
የኤርትራ መንግሥት በቀይ ባሕር አፋሮች ላይ እያደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ግፍ በሚመለከት ለአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ክስ መቅረቡን አብራርተዋል፡፡
ጥያቄው በኮሚሽኑ ተቀባይነት አግኝቶ የኤርትራ መንግሥት በ60 ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን ተናግረዋል፡፡
የኤርትራ መንግሥት በአፋር ሕዝቦች ላይ እያደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያወግዝም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ግልጽ ፣ቀልጣፋና የዘመነ እንዲሆን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ
የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ በመምህር ዳኪቶ ጋወቶ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ።
ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን በገዛ ሜዳው አሸነፈ