አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ቡርኪና ፋሶ ኢኳቶሪያል ጊኒን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
ቀን 9:30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ኤድመንድ ታፕሶባ እና ጆርጂ ሚኖንጎ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች።
ባሲሊዮ ንዶንግ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ የተሰናበተባት ኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቪን አኒየቦህ ባስቆጠራት ግብ እየመራች ቆይታ ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባት ግብ አሳዛኝ ተሸናፊ ሆናለች።
More Stories
ቼልሲ እና ዌስትሃም ዩናይትድ የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው
በጋርዲዮላ ለምን እንደተፈለገ እያሳየ የሚገኘው ዶናሩማ…
በግብ የታጀበው የሼሽኮ ፍጥነት