ማሻ፣ ታህሳስ 15/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትውልድን በስነ – ምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ አዲስ ለተመደቡና እና ለነባር የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተሮች ፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ቴፒ ግቢ በመስጠት ላይ ይገኛል ።
ሙስናና ብልሹ አሰራሮች የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማደናቀፍ በህዝብ እና በመንግሥት መካከል ያለውን ግኑኝነት በማሻከር በሀገር ዕድገት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን የሚያስከትሉ መሆናቸው ይታወቃል።
የክልሉ ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ በወቅቱ እንደገለፁት ሀብትን በተገቢው ማሳወቅና ማስመዝገብ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከል ባሻገር ግልፀኝነትን እንዲፈጠር ያለው ፍይዳ የጎላ በመሆኑ በትኩረት ሊሠራበት እንደሚገባ ነው የገለፁት ።
በክልሉ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስነ-ምግባር ትምህርት ሥርፀት ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ዘለቀ የሀብት ምዝገባ እና ማሳወቅ ዓላማዎችን ጨምሮ በአዋጆችና ደንበኞች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሲሰጡ ሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚረዳ ስልት ነው ብለዋል ።
የአሰራር ሥርዓት ጥናት መሠረታዊ ሀሳቦችንና ሂደትን መከተል ሌላኛው ሙስናን ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑን የገለፁት ደግሞ በክልሉ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስነምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይረክተሬት ወ/ሮ ጥሩእሸት ደቦጭ ናቸው ።
ስልጠናው የኮሚሽኑ አዋጆችና መመሪያ ፣ ሙስናና የጥቅም ግጭት ፣ሙስናን መከላከል ፣በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ማካሄድ እንዲሁም የአሰራር ጥናት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ።
More Stories
ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ዕድገት ማነቆ የሚሆኑ ችግሮች ተለይተው በዘላቂነት መፈታት አለባቸው፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
አሜሪካ እና ኢራን ግጭትን ሊያስቀር ይችላል የተባለውን ወሳኝ ውይይት ዛሬ ይጀምራሉ
የመራጮች ዲጂታል ምዝገባ ሥርዓት ለምርጫ ተአማኒነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል – ምሁራን