ማሻ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 ((ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ጃፓን የዓለማችን ትልቁን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዋን ከ15 ዓመታት በኋላ ዳግም ስራ ልታስጀምር ነው፡፡
ጃፓን በፈረንጆቹ 2011 በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥና ሱናሚ ምክንያት በፉኩሽማው የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዋ ላይ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ የኑክሌር ማብላያዎች ተዘግተው ቆይተዋል።
በዚህም ከውጪ ሀገራት ከምታስገባው የነዳጅ ምርት ያላትን ጥገኝነትን ለመቀነስ የተዘጉ የኑክሌር ጣቢያዎችን በድጋሚ የማስጀምር ስራዎችን እየሰራች ሲሆን እስካሁን 14 የኑክሌር ማብላያዎችን በድጋሚ ስራ አስጀምራለች፡፡
በዛሬው ዕለት ደግሞ በሀገሪቱ ኒጋታ ግዛት የሚገኘውን የካሺዋዛኪ ካሪዋ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያን በድጋሚ ስራ እንድታስጀምር የግዛቷ ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ውሳኔውን ተከትሎም የዓለማችን ትልቁ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በመጪው ጥር ወር ዳግም ስራ ይጀምራል መባሉን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
ጣቢያው የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል በሚሊየኖች ለሚቆጠሩ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን፥ በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የሚረዳ መሆኑን ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች የኑክሌር ኃይል ማመንጫው ስራ መጀመር የፉኩሽማ አይነት አደጋ ሊፈጠር ይችላል በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
#ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
ፕሬዚዳንት ታዬ ለፈረንጆች የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ሀብትን በተገቢው ማሳወቅና ማስመዝገብ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል ግልፀኝነት እንዲፈጠር ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለፀ ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን የቡና ልማት ሊያሳድግ የሚችለው ግዙፍ ፕሮጀክት